Publisher's Synopsis
"አንፈርስም አንታደስም" የደራሲ አሌክስ አብርሃም ሁለተኛ የግጥም መፅሐፍ ነው። መፅሐፉ ውስጥ የተካተቱት ግጥሞች ከስነፅሁፍ ውበታቸው ባለፈ የትውልዱን ጩኸት የሚያስተጋቡ ፣ አንዴ ካነበቧቸው ከአእምሮ የማይጠፉ ህያው ሐሳቦች ናቸው።
የደራሲ አሌክስ አብርሃም ግጥሞች በሬዲዮ ፕሮግራሞች ፣ በስነፅሁፍ መድረኮች፣ በተለያዩ አንባቢያን ከመቅረባቸውም በላይ በመነባነብ ፣ እንዲሁም በአንድ ሰው ተውኔት ስልት ተዘጋጅተው ከፍ ያለ አድናቆት ተችሯቸዋል። ደራሲ አሌክስ አብርሃም አጭር ልብወለዶች መፃፍ ከመጀመሩ በፊት በርካታ ግጥሞቹን በሬዲዮ በማቅረብ ይታወቃል።