Delivery included to the United States

ሐጂ ራሕመቶ ሙኽታር

ሐጂ ራሕመቶ ሙኽታር የሐጂ ራሕመቶ ሪጃቶ የሕይወት ታሪክ

Paperback (11 Dec 2024) | Afrikaans

  • $19.82
Add to basket

Includes delivery to the United States

10+ copies available online - Usually dispatched within 7 days

Publisher's Synopsis

የአባቴ ታሪክ እንዲፃፍ የምፈልገው ለሀገራቸው (ኢትዮጵያ) የለፉት ልፋት እና የነበራቸው ደግነት የልጅ ልጆቻቸው እና ሰፊው የኢትዮጰያ ሕዝብም እንዲያውቀው በማለት ነው፡፡ አባባ ለሀገራቸው በጣም ለፍተዋል፣ ደክመዋል፡፡ ዘር እና ሃይማኖት ሳይለዩ ደግነታቸውን እና ልግስናቸውን አሳይተዋል፡፡ ይህንን ሥራቸው እና ተግባራቸው ትውልድ እንዲያውቀው፣ እንዲማርበት፣ የበኩሉን መልካም ሚና እንዲወጣበት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
በመሆኑም ይህ ኪታብ (መጽሐፍ) መታተሙ ለእኔ ትልቅ ደስታ ነው፡፡ እኛ ልጆቻቸው፣ አሁንም ድረስ የልጅ ልጆቻቸው የምንኖረው አባባ እና እማማ (ሐጂ ራሕመቶ እና እማማ ራዲያ) በሠሩዋቸው በጎ ሥራዎች ነው (አላሃምዱሊላህ)፡፡
አባባ ለሀገር፣ ለሕዝብ፣ ለሃይማኖት እና ለባሕል የሠሩዋቸው መልካም ሥራዎች ተዘርዝረው የሚያበቁ ባይሆኑም በኪታቡ ውስጥ አንኳር-አንኳሮቹ ተጠቀሰዋል፡፡ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ለሀገር ልማት፣ ዕድገት እና ነፃነት ያደረገው ተጋድሎ በጥሩ ሁኔታ ያሳያል፡፡
ይህንን መልካም ሥራ (ታሪክ) እንዲጠና እና እንዲታተም ላደረጉ ልጆቻችን (ተሕያ ሐጂ ዑመር (ዶ/ር)፣ አብዱልመጂድ ሐጂ ዑመር፣ ሰለሃዲን ሐጂ ዑመር፣ ጀውሃር ሐጂ ዑመር፣ ዘይነብ ሐጂ ዑመር፣ በያን ሐጂ ዑመር፣ ሚናህ ኸድር ሐጂ ራሕመቶ)
ክብር እና ሞገስ ይግባቸው፡፡ ካወጡት ብዙ እጥፍ አላህ ይለግሳቸው፡፡
የመጽሐፉ አዘጋጅም ሊመሰገን ይገባል፡፡ በቤተሰባዊ እና በሀገራዊ መንፈስ ሥራውን በአጭር ጊዜ ሠርቶ አቅርቧል፡፡ በዕውቀቱ የሚጠቀም፣ ይበልጥ ለሀገር እና ለሕዝብ የሚሠራ አላህ እንዲያደርገው ዱዓ አደርጋለሁ፡፡

Book information

ISBN: 9798302205636
Publisher: Amazon Digital Services LLC - Kdp
Imprint: Independently Published
Pub date:
Language: Afrikaans
Number of pages: 278
Weight: -1g
Height: 229mm
Width: 152mm
Spine width: 15mm